Connect Arduino


1 | የአርዱኢኖ ቦርድና ኬብል አዘጋጅ 

በዚህ መለማመጃ  Arduino UnoArduino DuemilanoveNanoArduino Mega 2560 , ወይም  Diecimila እየተጠቀምክ እንደሆነ እናስብ። 
በተጨማሪም የፕርንተር አይነት ኬብል ወይም (A plug to B plug cable) ያስፈልግሀል። የአርዱኢኖህ ቦርድ አይነት ሚኒ ከሆነች ለምሳሌ (A to Mini-B cable) ወይም ትንሿ የስልክ ኬብል ታስፈልግሀለች። 
 

2 | የአርዱኢኖ ሶፍትዌር ዳውንሎድ አድርግ 

አዲሱን እትም ሶፍትዌር ከአርዱኢኖ ኦፊሺያል ሳይት  download page ዳውንሎድ አድርግ። 
ዳውንሎድ እንደጨረሰልህ ፋይሉን አንዚፕ አድርገህ ጡሩ ቦታ መርጠህ አስቀምጠው፣ ፎልደሩን ስትከፍተው ሌሎች ፎልደሮችና ፋይሎች ታገኛለህ; ሁሉም ባሉበት ይቀመጡ። 

3 | ቦርዱን አገናኝ 

Arduino Uno, Mega, Duemilanove እና Arduino Nano በቀጥታ ከUSB ፓወር ሲወስዱ  Arduino Diecimila ላይ ግን ማስትካከል የሚጠበቅብህ ነገር አለ፣ ከUSB አጠገብ ሶስት ፒኖች አሉ፣ ሁለቱ ፒኖች በፕላስቲክ ማጣመሪያ ተጣምረዋል፣ ፖወር ከUSB  ይወስድልህ ዘንድ ወደ USBው በኩል ያሉት ሁለት ፒኖች በፕላስትኩ ማጣመሪያ የተያያዙት መሆናቸውን አረጋግጥ፣ ካልሆነም ፕላስቲኩዋን ነቅለህ ሁለቱ ለ USB ቅርብ የሆኑት ፒኖች ላይ ሰካው።  

4 | ድራይቨሮችን መጫን 

የ Arduino Uno ወይም  Arduino Mega 2560 ቦርድ ድራይቨሮችን Windows7, Vista, ወይም XP ላይ መጫን 
ቦርድህን ሰካውና ዊንዶውስ ድራይቨር መጫን ሞክሮ እስለምያቅተው ጠብቅ፣ ልክ fail ሲያድርግ MY COMPUTER ላይ right click አድርግና manage የሚለውን click አድርግ፣ በግራ በኩል ከሚመጡት ዝርዝሮች device manager የሚለውን ምረት፣ በቀኝ ከሚያመጣው ዝርዝር ደግሞ (COM & LPT) የሚለውን ስትዘረዝረው በስሩ "Arduino UNO (COMxx)" የሚል ታገኛለህ፣ right click አድርግበትና "Update Driver Software" የሚለውን click አድርግ፣ ከዛ "Browse my computer for Driver software" የሚለውን ስትመርጥ ከቆምፒተርህ browse አንድታድርግ ይፈቅድልሃል፣ ቅድም ዳውንሎድ ካደረከው ሶፍትዌር ፎልደር ውሰደውና "Drivers" ከሚል ፎልደር ውስጥ "arduino.inf" የሚል ፋይል ምረጥለት፣ አለቀ። "FTDI USB Drivers" የሚለውን ፎልደር ተመሳስሎብህ አንዳትመርጥ ተጠንቀቅ። የምትጠቀመው ሶፍትዌር ቨርዥን 1.0.3 ወይም ከዚህ የበፊት ከሆነ "Arduino UNO.inf" የሚል ፋይል ትመርትለታለህ።

5 | አርዱኢኖ አፕሊኬሽንህን አስጀምር 

አርዱኢኖ ፎልደር ውስጥ ያለውን Arduino application Double-click አድርገህ አስጀምር . (Note: አርዱኢኖ ሶፍትዌርህ ባልፈለከው ቋንቋ ከከፈተብህ preferences ዳያሎግ ውስጥ ማስተካከል ትችላለህ; environment page ውስጥ ዝርዝር መረጃ አለልህ)

6 | LED መብራት blink አንዲያደርግ የሚያዘውን ኮድ ሞክር  

ወደ File > Examples > 1.Basics > Blink ሂደህ ክፈተው 

7 | ያንተን ቦርድ ምረጥለት

የምትሞክርበትን ቦርድ ለመምረጥ  Tools > Board ውስጥ ግባና ያንተን ቦርድ ምረት 
በስእሉ ላይ Arduino Uno ቦርድ ሲመረጥ ያሳያል 
Duemilanove Arduino ሁነው ATmega328 ቺፕ ለሚጠቀሙ ቦርዶች Arduino Duemilanove ወይም Nano w/ ATmega328.የሚሉትን ምረጥላቸው, (ቺፑ ATmega328  መሆኑን ለማወቅ ቦርዱ ላይ ያለውን ትልቅ IC ቁጥር ተመልከት) ከ ATmega168 ቺፕ ጋር ለሚመጡ አርዱኢኖ ቦርዶች Arduino Diecimila, Duemilanove, ወይም Nano w/ ATmega168 የሚለውን ምረጥለት። (በዚህ ጉዳይ የበለጠ ለማወቅ environment page አንብብ)

8 | Serial port ምረጥ 

ሜኑ ውስጥ ገብተህ ከዛ Tools/ Serial Port ሂድና ያንተን አርዱኢኖ ቦርድ Serial Port ምረጥ። ብዙውን ግዜ COM3 ወይም ከዛ በላይ ይሆናል (COM1 እና COM2 ለ hardware serial port ስለሚውል ነው) ይህን ለማወቅ አርዱኢኖህን ስትነቅለው አብሮ የሚጠፋው COM እሱ ያንተ አርዱኢኖ ነው ማለት ነው።

9 | አሁን ወደ አርዱኢኖህ ፕሮግራሙን Upload አድርግ 

በቀጥታ "Upload" በተኑን ተጫን፣ ትንሽ ሰከንዶች ታገስ;ቦርዱ ላይ የመቀበል-መላክ መብራቶቹ (RX እና TX LED) መጫወት ይጀምራሉ፣ ከተሳካ "Done uploading" የሚል ጽሑፍ status bar ላይ ይነበባል። (Arduino Mini, NG, ወይም ሌላ ቦርድ አየተጠቀምቅ ከሆነ አፕሎድ ከማዘዝህ በፊት ቦርዱ ላይ reset በተኑን መጫን እንዳትረሳ)
ከጥቂት ሰከንዶች ቡሃላ 13ኛው ፒን ስር ያለችው (L) የሚል ጽሑፍ ያላት LED በብርቱካናማ ቀለም blink ማድረግ ትጀምራለች። ይህን ካየህ አንኳን ደስ አለህ አርዱኢኖህን በተሳካ መልኩ መገልገል ጀምረሃል። ችግር ካጋጠመህ troubleshooting suggestions ሂድና ለጥያቄህ መልስ ፈልግ።
እነዚህንም ማየት ያስፈልግህ ይሆናል 
  • the examples for using various sensors and actuators
  • the reference for the Arduino language



1 comment:

  1. it's awesome how can i get all this staff in ethiopia?

    ReplyDelete