Official Arduino Tutorial and Distribution In Ethiopia.
የ አርዱኢኖ ኦፊሺያል ትርጉም ከማየታችን በፊት በራሳችን አገላለጽ ስናስቀምጠው:-
አርዱኢኖ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ አይነት ይዘት ያለው ቦርድ ሲሆን ለራሱ በተዘጋጀው ፕሮግራም ማድረጊያ ሶፍትዌር አማካኝነት ኮምፒውተርን በመጠቀም ፕሮግራም የመደረግ ችሎታ አለው:: ፕሮግራም የሚደረገውም ተጠቃሚው መጠቀም ለፈለገው ዲጂታል አገልግሎት ሁሉ ሲሆን፣ ለአርዱኢኖ የተዘጋጁትን የተለያዩ ሴንሰሮች አንደ input device መጠቀምና output ደግሞ አንደ relay, motor, LED, speakers, LCD... የመሳሰሉትን በተፈለገው መልኩ ከሴንሰሮች ዳታ እየተቀበለ ወይም የተጻፈለትን ዳታ አያነበበ ማንቀሳቀስ እንዲችል ተደርጎ ፕሮግራም ማድረግ ይቻላል ማለት ነው:: ይህ flexible ዕቃ ለፈለግነው robotic አይነት ሥራ መጠቀም እንችላለን ማለት ነው::
አርዱኢኖ እንደ ኦፊሺያል ትንታኔው ደግሞ እንዲህ ይሉታል:- አርዱኢኖ ለህዝብ ክፍት የሆኑ (open-source)
ኮዶችን በማገናዘብ አካባቢን ከሚያነፈንፉ (Sensors) መረጃን ተቀብሎ አካባቢ ላይ ተፅእኖ በሚሳድሩ ግብአቶች(output devices) በኩል ምላሽ የሚሰጥ በራሱ የቆመ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ነው፡፡
Official Arduino Tutorial and Distribution In Ethiopia.
የ አርዱኢኖ ኦፊሺያል ትርጉም ከማየታችን በፊት በራሳችን አገላለጽ ስናስቀምጠው:-
አርዱኢኖ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ አይነት ይዘት ያለው ቦርድ ሲሆን ለራሱ በተዘጋጀው ፕሮግራም ማድረጊያ ሶፍትዌር አማካኝነት ኮምፒውተርን በመጠቀም ፕሮግራም የመደረግ ችሎታ አለው:: ፕሮግራም የሚደረገውም ተጠቃሚው መጠቀም ለፈለገው ዲጂታል አገልግሎት ሁሉ ሲሆን፣ ለአርዱኢኖ የተዘጋጁትን የተለያዩ ሴንሰሮች አንደ input device መጠቀምና output ደግሞ አንደ relay, motor, LED, speakers, LCD... የመሳሰሉትን በተፈለገው መልኩ ከሴንሰሮች ዳታ እየተቀበለ ወይም የተጻፈለትን ዳታ አያነበበ ማንቀሳቀስ እንዲችል ተደርጎ ፕሮግራም ማድረግ ይቻላል ማለት ነው:: ይህ flexible ዕቃ ለፈለግነው robotic አይነት ሥራ መጠቀም እንችላለን ማለት ነው:: አርዱኢኖ እንደ ኦፊሺያል ትንታኔው ደግሞ እንዲህ ይሉታል:- አርዱኢኖ ለህዝብ ክፍት የሆኑ (open-source) ኮዶችን በማገናዘብ አካባቢን ከሚያነፈንፉ (Sensors) መረጃን ተቀብሎ አካባቢ ላይ ተፅእኖ በሚሳድሩ ግብአቶች(output devices) በኩል ምላሽ የሚሰጥ በራሱ የቆመ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ነው፡፡
ለአርት ሰዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ለተሰጥኦ ባለቤቶችና
ለማንኛውም ከአካባቢ ጋር የሚግባቡ እቃዎችን (interactive objects) መስራት ለሚፈልጉ ታሰቦ የተሰራ ነው፡፡
አርዱኢኖ ምን ይሰራል?
አርዱኢኖ አካባቢን ማነፍነፍ ከሚችሉ ግብአቶች (sensors) መረጃን በመቀበል እንደ
ዲናሞ መብራተና የመሳሰሉትን በመቆጣጠር ለአካባቢው አፀፋ የመስጠት ችሎታ አለው፡፡ ሰሌዳው ላይ ያለችው ጥንጥ-መቆጣጠሪያ (micro-controller) በአርዱኢኖ ፕሮግራም ማድረጊያ ቋነቋ መሰረት ፕሮግራም ይደረጋል፡፡ በአርዱኢኖ የሚሰሩ ፕሮጀከቶች በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ማድረግ፣
ወይም በኮምፒተር ውስጥ ከሚንቀሳቀስ ሶፍትዌር ጋር በጣምራ እንዲሰሩ ማድረግ ይቻላል፡፡ ምሳሌ ከነ (Flash,
Processing, MaxMSP) ጋራ፡፡
የአርዱኢኖ ቦርድ በግል መስራት የሚቻል ሲሆን የተሰራውንም መገዛት ይቻል ዘንድ አቅርበናል፡፡
ሶፍትዌሩን ደግሞ ከዚሁ በነፃ ዳውንሎድ ማድረግ የቻላል፡፡ ለሊኑክስና ሌሎች የዳውንሎድ ምርጫዎችም ከአርዱኢኖ ኦፊሺያል ሳይት በቂ አማራጮች አለልዎት።
አርዱኢኖ የ2006 Ars
Electronica Prix በዲጂታል ኮሙኒኬሽንስ ረድፍ የክብር ስምን አግኝቷል፡፡
አርዱኢኖን የሚስብ ከሚያደርጉት ነገሮች :-| ለህዝብ ክፍት የሆነ (open-source) |
አርዱኢኖ ዕቃው (ሃርድዌሩም) ሆነ ሶፍትዌሩ ክፍት ነው:: ለምሳሌ አርዱዕኖ ሃርድዌሩን መግዛት ያልፈለገ ሰው በራሱ መስራት ይችል ዘንድ (የአሰራር ማሳያ ስዕል) schematic ለሕዝብ ክፍት ተደርጎዋል::
| የመገጣጠም ችሎታው (connectivity) |

| የሚረዳህ ሰው ብዛት |
ሚሊዮኖች ግለሰብና ድርጅቶች የአርዱኢኖ ተጠቃሚዎች መሆናቸው አንተን ከስጋት ይገላግልሃል። ከ arduino.cc የህዝብ መተያየቂያ ፎረም አንስቶ እነ google+, facebook, twetter ላይ ብዙዎች አርስበርስ ይጠያየቃሉ፣ ሥራ ጀምረህ የከበደህን ለመጠየቅ የኪቦርድህን ቃላት ማሳመር ብቻ። አንዳዲስ ለመማርም youtube ላይ ያለው የ video መዓት ብቻ ብቂህ ነው።
| የአጠቃቀም ቅለት |
Arduino ፕሮግራም አደራረግ መሰረቱ processing ሲሆን፣ java እና መሰል ትምህርት ትንሽ የቀመሰ ሰው አርዱኢኖን ፕሮግራም አደራረግ መሰልጠን ምንም አያቅተውም። የመስራት የውስጥ ፍላጎት ያለው ሰው ደግሞ የተሳካለት የፈጠራ ሰው ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ።
ስለ አርዱኢኖ የበለጠ ጽሑፍና የቪዲዮ ስልጠና ለማግኘት የመረትንላችሁ ድረገጾች :-
- forum.arduino.cc
- bristolwatch.com/arduino
- element14.com
- instructables.com
- learn.adafruit.com/category/learn-arduino
- tronixstuff.com/
- exploring Arduino by Jeremy Blum